የሀገር ውስጥ ዜና

በሰራዊቱ የጀግንነት ተጋድሎ የገጠሙንን ውስብስብ አገራዊ አደጋዎች መመከት ችለናል-ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ

By Feven Bishaw

January 08, 2022

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 30፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሰራዊቱ የጀግንነት ተጋድሎ የገጠሙንን ውስብስብ አገራዊ አደጋዎች መመከት ችለናል ሲሉ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ተናገሩ፡፡

ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ፤ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ አቅራቢነት የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹሙ ጀነራል ብርሃኑ ጁላን ጨምሮ ለ101 የአገር መከላከያ ከፍተኛ የጦር መኮንኖች የማዕረግ እድገት ሰጥተዋል፡፡

የማእረግ እድገቱ በሰራዊቱ ዘንድ የኃይልና የሞራል የበላይነት ለመገንባት ፋይዳው የጎላ መሆኑን ማንሳታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡