አዲስ አበባ፣ ጥር 1፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የጀግኖቹ ሰማዕታት እሼቴ ሞገስ እና የልጃቸው ይታገሱ እሸቴ የቀብር ሥነ ሥርዓት በሸዋሮቢት ከተማ ተካሄደ፡፡
የሽኝት መርሃ-ግብሩ በመኖሪያ ቤታቸው ቤተሰቦቻቸው እና ወገን ዘመዶቻቸው እንዲሁም የመንግስት የሥራ ሃላፊዎች፣ የአማራ ክልል ልዩ ኀይል፣ ፋኖ እና ሚሊሻ በተገኙበት የተካሄደው፡፡
ለሀገር አንድነት ሲሉ መስዋዕት ለሆኑት አባት እና ልጁ አስከሬናቸው ከወደቀበት ቦታ ሳላይሽ ተነሥቶ በክብር ወደሚያርፍበት ሸዋሮቢት ደብረ ገነት ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን አሸኛኘት እየተደረገለት ነው፡፡
የሰሜን ሸዋ ዞን ምክትል አስተዳዳሪ አቶ ሲሳይ ወልደ አማኑኤል፥ አሸባሪው የህወሓት ወራሪ ሃይል በዞኑ በገባበት ወቅት እንደ እነ እሸቴ አይነቱ አባ ረፍርፍ ጀግኖች እና በሰራዊታችን ጀግንነት መደምሰሱን አውስተዋል፡፡
እንደ መንግስት የጀግናው እሸቴ ሞገስን አደራ ተቀብለን ከቤተሰቡ ጎን መሆናችንን እናረጋግጣለንም ብለዋል።
ጀግኖቹ እሸቴ ሞገስና ልጁ ይታገስ እሸቴ ለአገር ነፃነትና ለወገን ክብር ሲሉ የትሕነግ ወራሪ ኃይልን በመፋለምና በትንሹ 9 አሸባሪዎችን በመግደል ነው በክብር የተሰውት።
በግርማ ነሲቡ
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!