አዲስ አበባ፣ ጥር 1፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አገር ተረካቢ ወጣቱ ትውልድ በሀይማኖት በዘርና በፖለቲካ አመለካከት ሳይከፋፈል ኢትዮጵያን ከተደቀነባት አደጋ ለመታደግ የሀገር መከላከያ ሰራዊትና ልዩ ሃይሉን ሊቀላቀል እንደሚገባ የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ አካሉ ወንድሙ ተናገሩ፡፡
አቶ አካሉ እንደተናገሩት፥ “አባት አርበኞች በክብር ያቆዩልንን ጠንካራ ሀገር ልንጠብቅ፣ ጠላቶቿን እስከመጨረሻው እንድታሸንፍ ከፈለግን ከመንግስት ጎን በመሰለፍ መከላከያና ልዩ ሃይልን መቀላቀልና መታገል ይገባል”፡፡
በዛሬው ዕለት በደብረ ብርሃን ከተማ የፋኖ አደረጃጀትን የተቀላቀሉ በርካታ ወጣቶች ለሶስት ወራት የወሰዱትን ስልጠና አጠናቀው ተመርቀዋል።
ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በስፍራው ተገኝቶ ያነጋገራቸው ወጣት ሰልጣኞችም ፥ ‘’ሀገራችንን ከወራሪዎች ለማዳን የጸጥታ አደረጃጀቶችን በመቀላቀል የሚጠበቅብንን ድርሻ እንወጣለን’’ ብለዋል።
ታለ ማሞ
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!