የሀገር ውስጥ ዜና

በአማራ ክልል የሚተገበር የ4 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር ፕሮጀክት ይፋ ተደረገ

By Feven Bishaw

January 10, 2022

የአዲስ አበባ፣ ጥር 2፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አማራ መልሶ መቋቋምና ልማት ድርጅት ( አመልድ) በአማራ ክልል የሚተገበር የአምስት ዓመታት ፕሮጀክት ስምምነት ተፈራረመ፡፡

የድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር አለማየሁ ዋሴ ድርጅቱ ከለጋሽ አካላት ባገኘው የገንዘብ ድጋፍ አማካኝነት ለአምስት ዓመታት የሚተገበር የ4 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር ስምምነት ከተለያዩ ተቋማት የሥራ ኀላፊዎች ጋር ተፈራርመዋል፡፡