የሀገር ውስጥ ዜና

ዳያስፖራው እያመጣቸው ያሉ መድሃኒቶችና የህክምና ቁሳቁሶች በጥንቃቄ እንዲቀመጡ ተደርጓል

By Feven Bishaw

January 10, 2022

አዲስ አበባ፣ ጥር 2፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ዳያስፖራው ወደ አገር ቤት እያመጣቸው ያሉ መድሃኒቶችና የህክምና ቁሳቁሶች በተገቢው ጥንቃቄ ለአገልግሎት ምቹ ሆነው እንዲቀመጡ እየተደረገ መሆኑን የኢትዮጵያ የምግብና የመድሃኒት ቁጥጥር ባለስልጣን አስታወቀ።

የጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድን ጥሪ ተቀብለው በርካታ ዳያስፖራዎች ወደ አገር ቤት እየገቡ ሲሆን ፥ ወደ አገር ቤት ከገቡትም መካከል ብዙዎቹ በአሸባሪው ህወሃት ለወደሙ የጤና ተቋማት መድሃኒትና የህክምና ቁሳቁሶችን ይዘው መምጣታቸው ተገልጿል።