የሀገር ውስጥ ዜና

የህዝቡን የኑሮ ደረጃ ለማሻሻል በትኩረት ሊሠራ እንደሚገባ ተጠቆመ

By Feven Bishaw

January 10, 2022

አዲስ አበባ፣ ጥር 2፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በጋምቤላ ክልል የህዝብ ቁጥር ዕድገት ምጣኔንና የተፈጥሮ ሃብቶች ልማትን በማጣጣም የህዝቡን የኑሮ ደረጃ ለማሻሻል በትኩረት ሊሠራ እንደሚገባ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ቴንኩዌይ ጆክ ገለፁ።

የክልሉ ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ለክልሉ ካቢኔ አባላትና ለካቢኔ መስሪያ ቤቶች የልማት ዕቅድ ባለሙያዎች በስነ ህዝብ ዙሪያ ስልጠና ሠጥቷል።