የሀገር ውስጥ ዜና

ዳያስፖራው በቴክኖሎጂ ዘርፍ ባለው ልምድና እውቀት ሀገሩን እንዲደግፍ ጥሪ ቀረበ

By Meseret Awoke

January 11, 2022

አዲስ አበባ፣ ጥር 3፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ታላቁን ወደ ሀገር ቤት የመመለስ ጥሪን ተቀብለው ወደ ሀገራቸው የመጡ ዳያስፖራዎች ሀገራቸውን በሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ዘርፍ እንዲደግፉ ጥሪ አቅርቧል።

ሚኒስቴሩ ዳያስፖራዎች በዘርፉ ሀገራቸውን ለመደገፍ እና የኢንቨስትመንት አማራጮችን ማየት በሚቻልበት ጉዳይ ላይ በመጪው ሃሙስ ይመክራል።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ሁሪያ አሊ፥ የግሉን ዘርፍ እና የዳያስፖራውን አባላት ተሳትፎ የሚያጠናክር ፎረም በእለቱ እንደሚመሰረት ተናግረዋል።

ዳያስፖራው ኢትዮጵያ ላይ የሚደርሰውን አለም አቀፍ ጫና በመቃወም ያስመዘገበውን ውጤት ያደነቁት ሚኒስትር ዴኤታዋ ፥ በቴክኖሎጂው ዘርፍም ይህንን ታሪክ እንዲደግመው ጥሪ አቅርበዋል።

በመጪው ሃሙስ በሚካሄደው የምክክር መድረክ በዘርፉ ሀገራቸውን መደገፍ የሚችሉ ሁሉ እንዲሳተፉ ጥሪ መቅረቡን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!