የአዲስ አበባ፣ ጥር 3፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የጠቅላይ ሚኒስትሩን ጥሪ ተቀብለው ወደ አገር ቤት የመጡ የዳያስፖራ አባላት ኢንቨስትመንት ፎረም በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነዉ።
ዳያስፖራው በኢትዮጵያ የሚገኙ የኢንቨስትመንት አማራጮችንና እድሎችን በመጠቀም መዋዕለ ንዋዩን በማፍሰስ ለአገሩ ምጣኔ ሐብትና ብልጽግና አስተዋጽኦ ማድረግ የሚችልበትን ዕድል ለማመላከት ያለመ ፎረም መሆኑን የኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ሌሊሴ ነሜ ገልጸዋል።