የሀገር ውስጥ ዜና

ሀገራችን ውስብስብ ችግሮች ቢገጥሟትም ዕምቅ አቅም ያላት በመሆኑ ለወጣቶች ሥራ መፍጠር ይገባል – አቶ ንጉሡ ጥላሁን

By Feven Bishaw

January 11, 2022

አዲስ አበባ፣ ጥር 3፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ሀገራችን ውስብስብ ችግሮች ቢገጥሟትም ዕምቅ አቅም እና ትልቅ ተስፋ ያላት በመሆኑ በተለይ ከተሞች ላይ ዕድሎችን ተጠቅሞ ለወጣቶች ሥራ መፍጠር እንደሚገባ በሥራ እና ክህሎት ሚኒስቴር የሥራ፣ ሥራ ስምሪት እና ገበያ ዘርፍ ሚኒስትር ዲኤታ ንጉሡ ጥላሁን ገለጹ፡፡

በቀጣዮቹ አምስት ዓመታት በ11 ከተሞች 70 ሺህ ወጣቶችን አስልጥኖ የሥራ ዕድል ለማመቻቸት ፕሮጀክት ተቀርፆ እየተሰራ መሆኑ ተመላክቷል፡፡