አዲስ አበባ ጥር 3፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 11 ልዩ ስሙ ቱሪስት ኮንዶሚኒየም አካባቢ በግለሰብ ቤት ውስጥ በሁለት መጋዘን በሕገ-ወጥ መንገድ የተደበቀ ብዛት ያለው የሲጋራ ምርትና የመገናኛ ሬድዮ በፀጥታ ኃይሎች ተይዟል፡፡
በህብረተሰቡ ጥቆማ ብዛቱ 465 ካርቶን “ሻምላን” እና “ጎልደን” ሲጋራ፣ 5 ኩንታል ስኳር ፣ ኦባማ የጭነት መኪና እንዲሁም 1 የመገናኛ ሬድዮ በፀጥታ ኃይሎች መያዙ ተገልጿል፡፡