አዲስ አበባ፣ ጥር 4፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሐረሪ ክልል ከአፈፃፀም ጋር ተያይዞ እየታዩ የሚገኙ መሻሻሎችን ማጠናከር እንደሚገባ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ ተናገሩ፡፡
የክልሉ ካቢኔ ሲያካሄደው የቆየውን የተቋማት የ100 ቀናት እቅድ አፈፃፀም ግምገማ በዛሬው እለት አጠናቋል፡፡
በግምገማውም በክልሉ የሚገኙ ተቋማትና ተጠሪ ተቋማት በ100 ቀናት ያከናወኗቸው ተግባራትን በሚመለከት የአፈፃፀም ሪፖርት ለካቢኔው ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል፡፡
የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር አቶ ኦርዲን በድሪ በግምገማው ማጠቃለያ ላይ እንደተናገሩት፥ የታቀዱ እቅዶች አንፃር በተከናወኑ ተግባራት ውጤታማ ስራዎች ተሰርተዋል፡፡
በተለይም ካለፉት አመታት አንፃር እየታዩ ያሉ መሻሻሎችን ማጠናከርና የህዝብን ጥያቄ ሊመልሱ የሚችሉ ተግባራት ላይ መረባረብ ወሳኝ ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡
ከስራ እድል ፈጠራን በተመለከተም አሁንም የሁሉም ተቋማት ቁልፍ ስራ ማድረግ ያስፈልጋል ብለው፥ ከዚህ ቀደም ተገንብተው ወደ ስራ ያልገቡ ፕሮጀክቶች በአፋጣኝ ወደ ስራ እንዲገቡም ነው ያሳሰቡት፡፡
እንደ ሀገር የገጠሙ ችግሮችን ከመቅረፍ ጎን ለጎን በልማቱም ሆነ ኢኮኖሚው ዘርፍ በላቀ ትኩረትና ቁጭት መስራት አስፈላጊ ነው ያሉት የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳደር ወይዘሮ ሚስራ አብደላ ናቸው፡፡
በክልሉ ህገወጥ ግንባታና የመሬት ወረራ እንዲፈጸም በሚያደርጉ አካላት ላይ ተገቢውን እርምጃ እንደሚወሰድ ጠቁመው ፥ በተለይም ክልላዊ ገቢን ከማጎልበት አንፃር ርብርብ ማድረግ ተገቢ መሆኑን አመላክተዋል፡፡
የነበሩ ክፍተቶችን በማረምና አንድነት ሊያጠናክሩ የሚችሉ ተግባራት በማከናወን የህዝቡን አብሮነትን ማጎልበት ያስፈልጋል ሲሉ ተናግረዋል፡፡
ለሁለት ቀናት ሲካሄድ በቆየው የ100 ቀናት እቅድ ክንውን ግምገማ መድረክም በየዘርፉ የተነሱ ጥያቄዎች ከሚመለከታቸው ተቋማት ምላሽና ማብራሪያ እንደተሰጠበት ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!