የሀገር ውስጥ ዜና

በደብረ ብርሃን በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ ነዋሪዎችን የሚያሳትፍ የሴፍቲኔት ፕሮጀክት ተጀመረ

By Meseret Awoke

January 13, 2022

አዲስ አበባ፣ ጥር 5፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በደብረ ብርሃን ከተማ በ10 ነጥብ 8 ሚሊየን ብር በጀት በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ ከ1 ሺህ 600 የሚልቁ ነዋሪዎችን የምግብ ዋስትና በማረጋገጥና በስራ እድል ፈጠራ ተጠቃሚ የሚያደርግ የሴፍቲኔት ፕሮጀክት ተጀመረ።

የደብረ ብርሃን ከተማ ስራ እድል ፈጠራና ምግብ ዋስትና ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ግርማ ድባቤ ፕሮጀክቱ ከአለም ባንክ ጋር በትብብር የተጀመረ መሆኑን ገልፀዋል።

በከተማዋ ቀበሌ 02 እና 09 የተጀመረው ይህ ፕሮጀክት፥ በቀጣይ በተመረጡ ዘርፎች በሁሉም ቀበሌዎች የሚገኙ ነዋሪዎችን ተጠቃሚ ለማድረግ በትኩረት እንደሚሰራ ገልፀዋል።

በከተማ ሴፍትኔት ተጠቃሚ ከሆኑት መካከል ወይዘሮ መስታወት ጋሻው እና ማህሌት ሙሉጌታ የተፈጠረላቸው የስራ እድል ኑሯቸውን ለመቀየር እንደሚያግዝ ተናግረዋል።

የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ዘውዱ ከበደ በበኩላቸዉ፥ የሴፍትኔት ፕሮግራሙ በከተሞች ለሚገኙ ስራ አጥ ዜጎች የስራ ዕድል ከመፍጠር ባሻገር በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ያሉ ዜጎች የምግብ ዋስትናቸውን እንዲያረጋግጡ የሚያግዝ በመሆኑ ተገቢውን ክትትል እና ቁጥጥር እናደርጋለን ብለዋል።

በሰላማዊት ሙሉነህ

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!