የሀገር ውስጥ ዜና

በአጣዬ በአሸባሪዎቹ ሸኔና ህወሃት የወደሙ የመኖሪያ ቤቶችን ለመገንባት የመሰረት ድንጋይ ተቀመጠ

By Feven Bishaw

January 13, 2022

አዲስ አበባ፣ ጥር 5፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ካናዳውያን ኔትወርክ ለማህበራዊ ድጋፍ በጎ አድራጎት ድርጅት በአጣዬ ከተማ በአሸባሪዎቹ ሸኔና ህወሃት የወደሙ የመኖሪያ ቤቶችን ለመገንባት የመሰረት ድንጋይ አስቀመጠ።

የከተማዋ አስተዳድር ከንቲባ አሳልፍ ደርቤ እንደተናገሩት፥ በከተማዋ ህወሃትና ሸኔ በጋራ ሆነው 420 መኖሪያ ቤቶችና 50 ግሮሰሪና ሆቴሎችን አውድመዋል፤ ከ250 በላይ ሰዎችንም ገድለዋል።