የሀገር ውስጥ ዜና

ባለስልጣኑ ባለፉት ስድስት ወራት ከተለያዩ አገልግሎት ክፍያዎች ከ 914 ሚሊየን ብር በላይ ገቢ አገኘ

By Feven Bishaw

January 13, 2022

አዲስ አበባ፣ ጥር 5፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአሽከርካሪና ተሽከርካሪ ፈቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን ባለፉት ስድስት ወራት ከተለያዩ አገልግሎት ክፍያዎች ከ914 ሚሊየን ብር በላይ ገቢ አግኝቷል፡፡

ባለስልጣኑ፥ በ2014 ዓ.ም በግማሽ ዓመቱ ከአሽከርካሪና ተሽከርካሪ አገልግሎቶች 1 ቢሊየን 50 ሚሊየን ብር ገቢ ለመሰብሰብ አቅዶ ነው 914 ሚሊየን 799 ሺህ ብር ገቢ የተገኘው፡፡