የሀገር ውስጥ ዜና

የጌዴኦ ዞን በድርቅ የተጎዱ የቦረና ዞን ከብቶች በመቀበል የግጦሽ መሬት ላይ አሰማራ

By Meseret Awoke

January 14, 2022

አዲስ አበባ፣ ጥር 6፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ክልል የጌዴኦ ዞን በድርቅ የተጎዱ የቦረና ዞን የአርብቶ አደር ከብቶችን በመቀበል የግጦሽ መሬት ላይ አሰማርቷል፡፡

በጌዴኦ ዞን ገደብ ወረዳ በ10 ሺህ የሚቆጠሩ ከብቶች በግጦሽ መሬት ላይ ተሰማርተው ከድርቁ ጉዳት እያገገሙ ይገኛሉ።

በዞኑ የከተሰተው ድርቅ በዝናብ እጥረት የተፈጠረ መሆኑን አርብቶ አደሮቹ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተናግረዋል።

ወደ ዞኑ የመጡ ከብቶች ጤንነት መሻሻል ቢታይባቸውም በፊት ከነበረባቸው ጉዳት አንጻር በፍጥነት ማገገም እንዳልቻሉ እና አሁንም ክትባትና ክትትል እንደሚያስፈልጋቸው ተገልጿል።

“የጌዴኦ ዞን ገደብ ወረዳ ህዝብ ከብቶቻችንና እኛን ተቀብሎ ከድርቅ ለመታደግ ለሰራው ስራ ምስጋና ይገባዋል” ብለዋል አርብቶ አደሮቹ፡፡

አርብቶ አደሮቹ ከብቶቻቸውን ከያዓበልኦ፣ አሮሮና ዲሬ ወረዳዎች ወደ ገደብ ወረዳ እንዳመጡ የተናገሩ ሲሆን÷ ህዝቡ ከድርቁ ጉዳት እንዲወጡ የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል።

በቢቂላ ቱፋና ጌታቸው ሙለታ

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!