አዲስ አበባ፣ ጥር 12፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ውጫሌና ውርጌሳ ከተሞች በሽብር ቡድኑ ህወሓት ተቋርጦባቸው የቆየውን የኤሌክትሪክ ኃይል ዳግም ማግኘታቸውን የኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታወቀ፡፡
አሸባሪው የህወሓት ቡድን በኤሌክትሪክ መሰረተ ልማቱ ላይ ጉዳት በማድረስ ከፍተኛ ኪሳራ ካደረሰባቸው ከተሞች መካከል የሆኑት ውጫሌና ኡርጌሳ ተቋርጦባቸው የነበረውን የኤሌክትሪክ ኃይል በዛሬው ዕለት ዳግም አግኝተዋል፡፡