አዲስ አበባ፣ ጥር 12፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአሸባሪው የህወሃት ቡድን በተካሄደው ወረራ ከውስጥም ከውጭም ኢትዮጵያን የማፍረስረስ ግብ ያለውና ሚዲያዎችን በመጠቀም ጭምር ከባድ ሴራ የተጠነሰሰበት እንደነበር ምሁራን ተናገሩ፡፡
ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ቆይታ ያደረጉት የማህበራዊ ሳይንስ ባለሙያ ዘላለም ግዛቸው÷ኢትዮጵያ በውስጥም በውጭ የተደቀነባት ጫና በኢኮኖሚውና በፖለቲካው ዘርፍ ሚዲያዎችን በመጠቀም ጭምር ሀገሪቱን ለማፈራረስ ከባድ ሴራ የተወጠነበት እንደነበር ነው ያብራሩት፡፡ እነዚህ የውስጥና የውጭ ሃይላት በሌሎች ሀገራት ላይ ያደረጉትን የማፍረስ የሴራ ፖለቲካ ሸርበው ቢነሱም፥ ኢትዮጵያ ግን እንደሌሎቹ ሀገራት በቀላሉ የምትንበረከክ አገር እንዳልሆነች ዳግም አስመስክራለች ብለዋል፡፡