የሀገር ውስጥ ዜና

ከንቲባ አዳነች አቤቤ ታላቁ ሩጫ በሰላም እንዲጠናቀቅ ላደረጉ አካላት ምስጋና አቀረቡ

By Meseret Awoke

January 23, 2022

አዲስ አበባ፣ ጥር 15፣ 2014 (ኤፍ ቢሲ)የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ታላቁ ሩጫ በሰላም እንዲጠናቀቅ ላደረጉ እና ላስተባበሩ አካላት ምስጋና አቅርበዋል፡፡

ከተማችን አዲስ አበባ በርካታ ህዝብ የሚሳተፉባቸው ታላላቅ ሁነቶችን ባማረና በደመቀ ሁኔታ በማስተናገድ ላይ ትገኛለች ብለዋል ከንቲባዋ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት፡፡

ዛሬም በጠዋቱ 13ኛው ከተማ አቀፍ የባህል ፌስቲቫልና የከተማችን ግርማ ሞገስ የሆነው 21ኛውን የታላቁ ሩጫ ውድድር በርካታ ነዋሪዎች፣ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ዳያስፖራዎች፣ ዲፕሎማቶች እና የውጪ ሀገር ዜጎች በተሳተፉበት በደመቀ ሁኔታ ተከናውኗልም ነው ያሉት።

መርሃ ግብሩ ስኬታማ እንዲሆን ተሳትፎ ላደረጉ፣ ላስተባበሩ እና ድጋፍ ላደረጉ አካላትም ምስጋና አቅርበዋል ፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!