አዲስ አበባ፣ ጥር 17፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በዩክሬንና ሩሲያ መካከል የተፈጠረውን ውጥረት ለማርገብ ቱርክ ያሳየችው የአደራዳሪነት ሚና በሁለቱም ወገኖች ዘንድ ተቀባይነት ማግኘቱን አንካራ ገለፀች።
የቱርክ ፕሬዚዳንት ሬሲፕ ጣይብ ኤርዶኻን የተገኙበትና በወቅታዊ የሀገር ውስጥ እና የውጭ ግኑኝነት ጉዳዮች ላይ አተኩሮ በተካሄደ የገዢው ፓርቲ (ኤ ኬ) ስብሰባ ላይ እንደተገለፀው፥ ቱርክ በዩክሬንና ሩሲያ መካከል እየጠነከረ የመጣውን ውጥረት ለማርገብ ያሳየችውን የአደራዳሪነት ሚና ሁለቱም ወገኖች መቀበላቸው ተመልክቷል።