የሀገር ውስጥ ዜና

በባቢሌ ከተማ ከ4 ሚሊየን ብር በላይ የሚያወጡ የተለያዩ የኮትሮባንድ እቃዎች ተያዙ

By Meseret Demissu

January 27, 2022

አዲስ አበባ፣ ጥር 19፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በምስራቅ ሐረርጌ ዞን ባቢሌ ከተማ ከ4 ሚሊየን ብር በላይ የሚያወጡ የተለያዩ የኮትሮባንድ እቃዎች መያዛቸውን የዞኑ ፖሊስ ኮሚሽን ገለጹ፡፡

በኮሚሽኑ የኮሙዩኒኬሽንና ሚዲያ ዲቪዥን አስተባባሪ ኢንስፔክተር ቶሎሳ ጐሹ በተለይ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለጹት፥   ጥር 17 ቀን 2014 ዓ.ም ከምሽቱ  አራት ሰዓት አካባቢ በተለምዶ “ሻምቦ” የሚባል የጭነት መኪና የተለያዩ የኮትሮባንድ እቃዎችን ጭኖ ሲያዘዋውር ነው የተያዘው።

ተሽከርካሪው ከሶማሌ ክልል ተነስቶ ፊቅ በሚባለው መንገድ በኩል ሊያልፍ ሲል በባቢሌ ኬላ በከተማው ፖሊስና በኦሮሚያ ልዩ ኃይል  እንዲሁም በኅብረተሰቡ ጥቆማ  መያዙን ጠቁመዋል።

የተያዙት እቃዎች ግምታዊ ዋጋቸው ከ4 ነጥብ 1 ሚሊየን ብር  በላይ የሚያወጡ የተለያዩ የህፃናትና የአዋቂዎች አልባሳትና ጫማዎች ፣ የእጅ ጋሪ ጎማዎችና መለዋወጫዎች ናቸው ብለዋል ኢንስፔክተር ቶሎሳ።

የኮትሮባንድ እቃዎቹን ሲያዘዋውር የነበረው አሽከርካሪ በቁጥጥር ሥር ውሎ የተያዙት እቃዎች በሐረር ደከር ጉሙሩክ መቆጣጠሪያ ጣቢያ ገቢ መደረጉም ነው የተገለጸው።

በተሾመ ኃይሉ

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን