የሀገር ውስጥ ዜና

ምክር ቤቱ የቀረበለትን የፌደራል መንግስት 122 ቢሊየን ብር ተጨማሪ በጀት አፀደቀ

By Mekoya Hailemariam

January 28, 2022

አዲስ አበባ፣ ጥር 20፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ)  የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቀረበለትን የፌደራል መንግስት 122 ቢሊየን ብር ተጨማሪ በጀት አፀደቀ ።

ተጨማሪ በጀቱ ለሀገር ደህንነት ማስጠበቂያ፣ ለሰብአዊ እርዳታ፣ በጦርነትና ግጭቶች ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች ማቋቋሚያ እንዲሁም ለሌሎች አስፈላጊ የመንግስት ስራዎች ማስፈጸሚያ የሚውል ነው ተብሏል፡፡

 

በፀጋዬ ወንደሰን