አዲስ አበባ፣ ጥር 20፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሺዴ የተመራው የኢትዮጵያ የልኡካን ቡድን ከሳውዲ አረቢያ የንጉስ ሰልማን የሰብአዊ እርዳታ ማእከል የበላይ ሀላፊ ከዶ/ር አብዱላህ አልራቢሀ ጋር በሁለቱ ሀገራት የጋራ ሰብአዊና የእርዳታ ጉዳዮች ላይ መክረዋል፡፡
ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሺዴ፥ ከሳውዲ ልማት ፈንድ ስራ አስኪያጅ ሱልጣን አልማርሻድ ጋርም ተገናኝተው የተወያዩ ሲሆን፥ በሳውዲ ልማት ፈንድ የገንዘብ ድጋፍ በኢትዮጵያ የሚያካሄዱትን የልማት ፕሮግራሞችና ፕሮጀክቶች ያሉበትን ሁኔታ በጋራ ገምግመዋል፡፡