የሀገር ውስጥ ዜና

ወልድያ፣መርሳ፣ ውጫሌ እና በአካባቢያቸው ባሉ ከተሞች የኤሌክትሪክ ኃይል መቋረጡ ተገለፀ

By Feven Bishaw

January 28, 2022

አዲስ አበባ፣ጥር 20፣2014 (ኤፍ ቢሲ) በ66 ኪሎ ቮልት ኤሌክትሪክ አስተላላፊ መስመር ተሸካሚ ምሰሶ ላይ በደረሰ የእሳት አደጋ ወልድያ፣ መርሳ፣ ውጫሌ እና በአካባቢያቸው ባሉ ከተሞች የኤሌክትሪክ ኃይል መቋረጡን የአማራ ክልል ኤሌክትሪክ  አገልግሎት አስታውቋል፡፡

ከደሴ ማከፋፈያ ጣቢያ እስከ ወልድያ ማከፋፋያ ጣቢያ በተዘረጋው 66 ኪሎ ቮልት የኤሌክትሪክ አስተላላፊ መስመር ላይ ሀብሩ ወረዳ ቀርጨም በር ቀበሌ አካባቢ በባለ አራት ቋሚ ምሰሶ ላይ ባልታወቀ ምክንያት በደረሰ የእሳት አደጋ ምሶሶዎቹ ሙሉ በሙሉ በመቃጠላቸው ወልድያ፣ መርሳ፣ውጫሌ እና በአካባቢያቸው ባሉ ከተሞች የኤሌክትሪክ ኃይል ተቋርጦባቸዋል፡፡