የሀገር ውስጥ ዜና

የጀግናው ኮሎኔል በዛብህ ጴጥሮስ የማስታወሻ ሐውልት ተመረቀ

By Feven Bishaw

January 30, 2022

አዲስ አበባ፣ ጥር 22፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ እርስቱ ይርዳ እና የኢፌዲሪ አየር ሀይል ዋና አዛዥ ሌተናል ጀነራል ይልማ መርዳሳ በሆሳዕና ከተማ የተገነባውን የጀግናው ኮሎኔል በዛብህ ጴጥሮስን የማስታወሻ ሐውልት መርቀው ከፈቱ፡፡

በምረቃ መርሐ ግብሩ የደቡብ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ጥላሁን ከበደ፣ የክልሉ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች፣ የኮሎኔል በዛብህ ጴጥሮስ ቤተሰቦች፣ የቀድሞ የአየር ኃይል ባልደረቦችና ጥሪ የተደረገላቸው ተጋባዥ እንግዶች ተገኝተዋል።