የሀገር ውስጥ ዜና

በርዕሰ-መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ የተመራው ቡድን በኦሮሚያ ክልል ጢዮ ቀበሌ የለማውን የስንዴ መስኖ ጎበኘ

By Alemayehu Geremew

January 30, 2022

አዲስ አበባ፣ ጥር 22፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ የተመራው ቡድን በምስራቅ ሸዋ ዞን አዳማ ወረዳ ጢዮ ቀበሌ የሚገኘውን የመስኖ ልማት ጎበኙ።

ቡድኑ የጎበኘው በምስራቅ ሸዋ ዞን አዳማ ወረዳ፣ ጢዮ ቀበሌ፣ ዋቄ በተባለ ቦታ በ641 ሄክታር መሬት ላይ የለማውን የስንዴ ማሳ ነው፡፡

የስንዴ ማሳውን 826 አርሶ አደሮች ተደራጅተው በክላስተር እያለሙ እንደሚገኝ ከኦሮሚያ ክልል ርዕሰ-መስተዳድር ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡