የሀገር ውስጥ ዜና

“የፓርቲያችንን እሴት በመጠበቅ ለክልላችን ብልፅግና እንተጋለን” – አቶ ኦርዲን በድሪ

By Meseret Awoke

February 01, 2022

አዲስ አበባ፣ ጥር 24፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) “የፓርቲያችንን እሴት በመጠበቅ ለክልላችን ብልፅግና እንተጋለን” ሲሉ የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ ገለጹ፡፡

የሀረሪ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች የአመራር ግንባታ የውይይት መድረክ መካሄድ ጀምሯል፡፡

የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪን ጨምሮ የክልሉ ብልፅግና ፓርቲ ኃላፊ አቶ አብዱጀባር መሀመድ እና ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች በተገኙበት ለመድረኩ በተዘጋጀው ሰነድ ላይ ውይይት እየተካሄደ መሆኑ ተገልጿል።

ብልፅግና ፓርቲ አሁን በተጀመረው የአመራር ግንባታ አካሄድ ብቁ አመራር እየገነባ፥ የጠራ እሳቤ ይዞ እንደሚወጣ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ገልጸዋል።

ህዝብ የማገልገል ሃላፊነትን በብቃት ለመወጣት የአገልጋይነት መንፈስን ተላብሶ አገራዊ ሃላፊነትን በአግባቡ የሚወጣ አመራር ማብቃት ያስፈልጋል ነው ያሉት አቶ ኦርዲን ።

“የፓርቲያችንን እሴት በመጠበቅ ለክልላችን ብልፅግና እንተጋለን” ሲሉም ተናገረዋል።

የውይይት መድረኩ ዋና አላማ በየደረጃው የሚገኘውን የፓርቲውን አመራር መገንባት መሆኑን የክልሉ ብልፅግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አብዱጀባር መሀመድ ገልጸዋል።

የአመራሩን የተግባር ጥንካሬና የፓርቲ ስነ ምግባር ከፍ በማድረግ የእያንዳንዱ አመራር ጥንካሬ እየጎለበተ ድክመት የሚታረምበት መድረክ መሆኑንም ከክልሉ ኮሙዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ፓርቲው የመልካም አስተዳደር ችግሮችን የመፍታት እና በቅንነት የማገልገል አቅም መፍጠር ፣ እንዲሁም ሀገራዊ እና የፓርቲ ተልዕኮን በብቃት መወጣት የሚችል አመራር እና አባል የማብቃት፣ የመገንባት እና የማጥራት ሂደት አካል መሆኑን ገልጸዋል።

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!