አዲስ አበባ፣ ጥር 24፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሺዴ ከሳዑዲ አረቢያ የገንዘብ ሚንስትር መሀመድ ቢን አብደላህ አል ጀዳን ጋር ተወያይተዋል::
በገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሺዴ የተመራ እና ከመንግስት የስራ ሃላፊዎች እና የሃይማኖት ተቋማት መሪዎች የተውጣጣ የኢትዮጵያ ከፍተኛ ልዑካን ቡድን የሁለቱ ሃገራት ግንኙነት የበለጠ ስለሚጠናከርበት እንዲሁም በሳዑዲ ዓረቢያ የሚገኙ ዜጎች የአጭር ጊዜና ዘላቂ መፍትሄዎች ስለሚያገኙበት ሁኔታ ከከፍተኛ ባለስልጣናት ለመምከር አልሞ ወደ ሳዑዲ አረቢያ ማቅናቱ ይታወሳል፡፡