የሀገር ውስጥ ዜና

በቄለምና ምዕራብ ወለጋ ዞኖች የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና እየተሰጠ ነው

By Meseret Demissu

February 01, 2022

አዲስ አበባ፣ ጥር 24፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በቄለምና ምዕራብ ወለጋ ዞኖች በጸጥታ ችግር ምክንያት ተራዝሞ የነበረው የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ዛሬ መሠጠት መጀመሩን የዞኖቹ ትምህርት ፅህፈት ቤቶች አስታወቁ።

በቄለም ወለጋ ዞን በ12 ወረዳዎችና በምዕራብ ወለጋ ዞን በቤጊና ቆንዳላ ወረዳዎች ከ15 ሺህ በላይ ተማሪዎች ፈተናውን በመውሰድ ላይ መሆናቸውን ፅህፈት ቤቶቹ አስታውቀዋል።

ፈተናው ዛሬን ጨምሮ ለአራት ቀናት እንደሚሰጥ አመልክተዋል።

የቄለም ወለጋ ዞን የትምህርት ቤቶች ፅህፈት ቤት ምክትል ሃላፊ ኤፍሬም ተፈራ ፥ በዞኑ በ12 ወረዳዎች በ42 የፈተና ጣቢያዎች ለ 14ሺህ228 ተማሪዎች ፈተናው እየተሰጠ ይገኛል።

ፈተናውን ይወስዳሉ ተብለው ከሚጠበቁት 16ሺህ 608 ውስጥ 1ሺህ 243 ተማሪዎች በተለያዩ ምክንያቶች ለፈተናው እንዳልተቀመጡ ሃላፊው ገልጸዋል።

የምዕራብ ወለጋ ዞን የትምህርት ቤቶች ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ዮናስ እምሩ በበኩላቸው ፥ የቤጊና ቆንዳላ ወረዳዎች የሚገኙ 1ሺህ137 ተማሪዎች በመንዲ ከተማ በተዘጋጁ አራት ጣቢያዎች ፈተናውን እየወሰዱ መሆናቸውን ተናግረዋል።

ፈተናውን እየወሰዱ ካሉ ተማሪዎች መካከል 118ቱ የግል ተፈታኞች መሆናቸውንም አመልክተዋል።

“በተለያዩ ምክንያቶች 931 ተማሪዎች ለፈተና መቀመጥ አልቻሉም” ም ማለታቸውን ኢቢሲ ዘግቧል።

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!