የሀገር ውስጥ ዜና

በአጭር ጊዜ ውስጥ የተቸገሩ ማኅበረሰቦችን በመደገፍ የአየር ንብረት ለውጡን መፋለም አስፈላጊ ነው- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ

By Feven Bishaw

February 03, 2022

አዲስ አበባ፣ ጥር 26፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአጭር ጊዜ ውስጥ የተቸገሩ ማኅበረሰቦችን በመደገፍ የአየር ንብረት ለውጡን መፋለም አስፈላጊ ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ገለጹ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እንዲሁም የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት ሽመልስ አብዲሳን ያካተተ ከፍተኛ የመንግሥት አመራሮች ቡድን በቦረና ዞን ያቤሎ ወረዳ በድርቅ የተጎዱ ማህበረሰቦችን ተግዳሮቶች በጥልቀት ለመገምገም ጉብኝት አካሂደዋል።