የሀገር ውስጥ ዜና

የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ለአማራ ክልል የ14 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ

By Feven Bishaw

February 03, 2022

አዲስ አበባ፣ ጥር 26፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ከተጠሪ ተቋማቱ ጋር በመሆን በአማራ ክልል በአሸባሪው የህወሓት ቡድን የተፈናቀሉ ወገኖችን መልሶ ለማቋቋም እና የወደሙ ንብረቶች መልሶ ለመገንባት የሚውል የ14 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ።

አሸባሪው ቡድን በወረራ ይዟቸው በነበሩ የአማራ ክልል አካባቢዎች የተፈናቀሉ ወገኖችን መልሶ ለማቋቋም የፌዴራል ሚኒስትር መስሪያ ቤቶች የተለያዩ ድጋፎችን እያደረጉ መሆኑ ተገልጿል።