የሀገር ውስጥ ዜና

የማላዊ ፕሬዚዳንት በአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ አዲስ አበባ ገቡ

By Feven Bishaw

February 03, 2022

አዲስ አበባ፣ ጥር 26፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የማላዊ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ላዛሩስ ማካርቲ ቻክዌራ በ35ኛዉ የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ አዲስ አበባ ገብተዋል።

ፕሬዚዳንቱ ቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱም የኢፌዲሪ የባህልና ስፖርት ሚኒስትር አቶ ቀጀላ መርዳሳ፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት አምባሳደር ብርቱካን አያኖ እንዲሁም የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የስራ ኃላፊዎችአቀባበል አድርገዉላቸዋል።