የሀገር ውስጥ ዜና

35ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ ባለሁለት እግር ሞተር ብስክሌት ማሽከርከር ተከለከለ

By Feven Bishaw

February 03, 2022

አዲስ አበባ፣ ጥር 26፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) 35ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ ባለሁለት እግር ሞተር ብስክሌት ማሽከርከር ፍጹም የተከለከለ መሆኑን የፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ- ኃይል አስታወቀ፡፡

የፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ ኃይል ከአዲስ አበባ ከተማ መንገድና ትራንስፖርት ቢሮ ጋር በጋራ በወሰነው መሰረት አሁን ያለውን የፀጥታ ሁኔታ በተገቢው ለመምራትና ለእንግዶቹ አስፈላጊውን አቀባበል ለማድረግ እንዲሁም የትራፊክ ፍሰቱን የተሳለጠ ለማድረግ ከነገ አርብ ጥር 27 ቀን 2014 ዓ/ም ጀምሮ ለሦስት ቀናት ባለሁለት እግር ሞተር ብስክሌትን በማንኛውም ሰዓት ማሽከርከር ፍፁም የተከለከለ መሆኑ ተገልጿል።