የሀገር ውስጥ ዜና

የአገር መከላከያ ተቋም በጦርነት ተጠምዶ ቢቆይም ጎን ለጎን በርካታ የልማት ስራዎችን አከናውኗል – ዶክተር አብርሃም በላይ

By Feven Bishaw

February 03, 2022

አዲስ አበባ፣ ጥር 26፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) “የአገር መከላከያ ተቋም በጦርነት ተጠምዶ ቢቆይም ጎን ለጎን በርካታ የልማት ስራዎችን አከናውኗል” ሲሉ የአገር መከላከያ ሚኒስትር ዶክተር አብርሃም በላይ ገለጹ።

ተጠሪነታቸው ለመከላከያ ሚኒስቴር የሆኑ ክፍሎች የ2014 ዓ.ም የ6 ወር እና የመቶ ቀን የስራ አፈፃፀም ግምገማ የተካሄደ ሲሆን ÷የአገር መከላከያ ሚኒስትር ዶክተር አብርሀም በላይ እና ሌሎች የመከላከያ ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል።