አዲስ አበባ፣ ጥር 29፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በዛሬው ዕለት ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክስርስቲያን ፓትሪያርክ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ ጋር ተወያይተዋል፡፡
ውይይታቸውን አስመልክተው ከንቲባዋ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው÷ ዛሬ ከብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ ፓትርያሪክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘ ኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘ አክሱም ወጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ጋር የተሳካ ውይይት አድርገናል ብለዋል።