አዲስ አበባ፣ ጥር 30፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አፍሪካ የሚያስፈልጋትን አንድ ጠንካራ አፍሪካዊ ሚዲያ እውን ለማድረግ በጋራ መስራት ይገባል ሲሉ በ35ኛው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባኤ ላይ የታደሙ ጋዜጠኞች ተናገሩ።
ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፓሬት ጋር ቆይታ ያደረጉት ለአፍሪካ 24 (Africa24) በግሉ የሚጽፈው አህመድ ኢብራሂም እና የሲ ጅ ቲ ኤን ዘጋቢው ግሩም ጫላ፥ የአፍሪካን እውነታ እና ብዝሃ ማንነት ለተቀረው ዓለም ለማስረዳት ጠንካራ ሚዲያ መገንባት ይገባል ብለዋል።