አዲስ አበባ፣ የካቲት 1፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የልምድ ልውውጥ ለማድረግ ኢትዮጵያ የገባው የናይጄሪያ መንግስት ልዑካን ቡድን ኢንዱስትሪ ፓርኮችን እየጎበኘ ነው፡፡
በናይጄሪያ የግብርና ሚኒስትር ሙሃመድ ማሃሙድ አቡበከር የተመራው ልኡክ 7 የግዛት አስተዳደር ኃላፊዎችን ጨምሮ 30 አባላት አሉት፡፡
የልዑኩ አባላት ቡልቡላ የተቀናጀ አግሮ ኢንዱስትሪ ፓርክን የጎበኙ ሲሆን ፥ ይርጋለም አግሮ-ኢንዱስትሪ ፓርክን እንደሚጎበኙ ከኢንደስትሪ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!