የሀገር ውስጥ ዜና

ኢንስቲትዩቱ የኩፍኝ ወረርሽኝ በተለያዩ ቦታዎች እየጨመረ መምጣቱ አሳሳቢ ነው አለ

By Meseret Awoke

February 08, 2022

አዲስ አበባ፣ የካቲት 1፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኩፍኝ ወረርሽኝ በተለያዩ ቦታዎች እየጨመረ መምጣቱ አሳሳቢ መሆኑን የደቡብ ክልል የኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዳይሬክተር አቶ ማሙሽ ሁሴን ገለጹ፡፡

የኩፍኝ ወረርሽኝን ለማስቆም የክትባት ጥራት፣ ፍትሐዊነትና ተደራሽነትን ማሻሻል ቁልፍ ተግባር መሆኑን ኢንስቲትዩቱ አስታውቋል ።

ኢንስቲቲዩቱ በክልል ደረጃ ኩፍኝ በወረርሽኝ መልክ ከተከሰተባቸው አካባቢዎች ጌዴኦ ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ደቡብ ኦሞ እንዲሁም በአሌ ልዪ ወረዳ መሆናቸውን ጠቁሟል፡፡

የደቡብ ክልል የኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ ማሙሽ ሁሴን እንዳሉት፥የኩፍኝ በሽታ በቀላሉ ከሰው ወደ ሰው በፍጥነት የሚዛመት በመሆኑ ፈጣን ተግባራዊ ምላሽ ያሻዋል፡፡

ወረርሽኙን በመከላከል በተከናወኑ ተግባራት ውጤት የተመዘገበ ቢሆንም ፥ ወረርሽኙ በተለያዩ ቦታዎች እየጨመረ መምጣቱ አሳሳቢ መሆኑንም ነው ዋና ዳይሬክተሩ ያመላከቱት።

በቀላሉ በክትባት መከላከል በሚቻል ወረርሽኞች የሰዎች ሕይወት ማለፍ እንደሌለበት ጠቁመው ፥ የወረርሽኙን ስርጭት ለመከላከል የክትባት ጥራትና ፍትሃዊነትን ማረጋገጥ እንደሚገባ ዳይሬክተሩ መግለጻቸውን ከክልሉ ጤና ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል ።

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!