አዲስ አበባ፣ የካቲት 2፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በዓለም አቀፍ ደረጃ በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ400 ሚሊየን አለፈ፡፡
የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ከተከሰተ ጀምሮ በዓለም አቀፍ ደረጃ በማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ ዘርፈ ብዙ ጫና እያሳደረ ይገኛል፡፡
አሁን ላይም ቫይረሱ በዓለም ዙሪያ ከ400 ሚሊየን በላይ ሰዎች ላይ የተገኘ ሲሆን ፥ ከዚህም የሚልቁ ሰዎች በቫይረሱ ሊያዙ እንደሚችሉ ነው የጆን ሆፕኪንስ ዩኒቨርሲቲ መረጃ የጠቆመው፡፡
እንደ ዩኒቨርሲቲው ስታስቲክሳዊ መረጃ ÷ እስካሁን 5 ነጥብ 8 ሚሊየን የሚጠጉ ሰዎች በቫይረሱ ሳቢያ ለህልፈት ተዳርገዋል፡፡
በአንጻሩ በዓለም አቀፍ ደረጃ ከ321 ሚሊየን 66 ሺህ በላይ ዜጎች ከቫይረሱ ማገገማቸው ነው የተገለጸው፡፡
አሜሪካ፣ ህንድ፣ ብራዚል፣ ፈረንሳይ እና ብሪታንያ ቫይረሱ ከጸናባቸው አገራት መካከል መሆናቸውን መረጃዎች ይጠቁማሉ።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!