አዲስ አበባ፣የካቲት 2፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አሸባሪው ህወሓት በአማራ እና በአፋር ክልሎች በሚገኙ የኤሌክትሪክ መሠረተ ልማቶች ላይ ከ 1 ቢሊየን 644 ሚሊየን ብር በላይ ውድመት ማድረሱን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስታወቀ፡፡
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር ሞገስ መኮንን በሰጡት መግለጫ ÷ ቡድኑ በአማራ እና አፋር ክልሎች ላይ በፈጸመው ወረራ በህዝብ ሃብት ላይ ከፍተኛ ውድመት አድርሷል ብለዋል፡፡
መሠረተ ልማቶችን መልሶ ለመጠገንት በተደረገው ጥረትም አብዛኞቹ የአማራ እና የአፋር ክልሎች የኤሌክትሪክ ኃይል ማግኘታቸውን ነው የገለጹት።
የወደሙ እና ዝርፊያ የተፈጸመባቸውን መልሶ በመጠገን የኅብተረሰቡን የኤሌክትሪክ ፍላጎት ለማሟላት ጥረት ተደርጓል ያሉት ዳይሬክተሩ÷ የወደመውን መሠረተ ልማት አሟልቶ ወደ ቀደመ አቅሙ ለመመለስ 23 ሚሊየን የአሜሪካን ዶላር እንደሚጠይቅ ተናግረዋል፡፡
አሸባሪው የህወሓት ቡድን በተጠቀሱት አካባቢዎች 53 ነጥብ 3 በመቶ የከፍተኛ ኃይል ማስተላለፊያ መስመሮች ላይ ውድመት ማድረሱም ተመላክቷል፡፡
በምስክር ስናፍቅ