የሀገር ውስጥ ዜና

የኢፌዲሪ ፕሬዚዳንትና የተመድ ምክትል ዋና ፀሐፊ በሽብር ቡድኑ ጉዳት የደረሰባቸውን ህፃናት ጠየቁ

By Feven Bishaw

February 09, 2022

አዲስ አበባ፣የካቲት 2፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዲሪ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ምክትል ዋና ፀሐፊ አሚና መሐመድ በአሸባሪው የህወሃት ቡድን ጉዳት የደረሰባቸውን ህፃናት ዱብቲ ሆስፒታል በመገኘት ጠየቁ።

ህፃናቱ ጉዳት የደረሰባቸው የሽብር ቡድኑ በተኮሰው ከባድ መሳሪያ መሆኑ ተገልፆላቸዋል።