አዲስ አበባ፣ የካቲት 6፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አሸባሪው እና ወራሪው የህወሓት ቡድን በአፋር ክልል ክልበቲ ረሱ ዞን እያደረሰ ያለውን ጥቃት አጠናክሮ መቀጡን ነዋሪዎች ተናግረዋል፡፡
የሽብር ቡድኑ በአፋር ክልል ክልበቲ ረሱ አካባቢ ባደረሰው ወረራና ጥቃት የአበአላ፣ ኮናባ፣ እሪፕቲ ፣ መጋሌ እና በረሃሌ ወረዳ ነዋሪዎችን ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለዋል፡፡
አሁን ላይም በሽብር ቡድኑ ጥቃት የተፈናቀሉ ዜጎች በኮሪ ወረዳ ጉዋህ ቀበሌ ተጠልለው እንደሚገኙ ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በስፍራው ተገኝቶ ተመልክቷል።
የሽብር ቡድኑ በማህበረሰቡ ላይ እየፈጸመ ባለው የከባድ መሳሪያ ጥቃትም ለከፍተኛ ሰቆቃ መዳረጋቸውን ነው ተፈናቃዮቹ የገለጹት።
ወራሪው ቡድኑ እያደረሰ ባለው ጥቃት ቤተሰብ ከቤተሰቡ ጋር ተለያይቶ መገናኘት እንዳይችል ማድረጉንም ነዋሪዎቹ ያስረዳሉ።
ወራሪውን ቡድን እያደረሰ ያለውን ጥፋት መንግስት እና የሚመለከተው አካል ዝም ሊለው እንደማይገባም ጠቁመዋል፡፡
የሰብዓዊ ድጋፍ ከማድረግ አንጻርም ትልቅ ትኩረትን እንደሚሻ እና በዘርፉ የተሰማሩ አካላት የበኩላቸውን እንዲወጡ ተፈናቃዮቹ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
በይስማው አደራው
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!