አዲስ አበባ፣ የካቲት 7፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ከአፍሪካ ልማት ፈንድ የ11 ነጥብ 48 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ ጸደቀለት።
ድጋፉ የፀደቀው የአፍሪካ ህብረት ምክር ቤት 35ኛው መደበኛ ጉባኤ በኢትዮጵያ ከተካሄደ ከጥቂት ቀናት በኋላ ነው።
የአፍሪካ ህብረት ይህንን እርዳታ አስተዳደሩን ለማጠናከር እና ተቋማዊ ዕድገት ለማድረግ ሊጠቀምበት ማሰቡ ተገልጿል።
ድጋፉ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን የ2063 አጀንዳን አቅምን ለማሻሻል ለተዘጋጀው ለአፍሪካ ህብረት ፕሮጀክት ተቋማዊ አቅም ግንባታ አስተዋፅኦ ያደርጋልም ተብሏል።
የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ምክትል ሊቀመንበር ዶክተር ሞኒክ ንሳንዛባጋንዋ÷ ከአፍሪካ ልማት ባንክ ፕሬዚዳንት አኪንዉሚ አዴሲና ጋር ስለ ድርጅቱ የወደፊት ሁኔታ እና ተግዳሮቶች ተወያይተዋል፡፡
ንሳንዛባጋንዋ ለተደረገው ድጋፍ አድናቆታቸው ገልፀው ፥ ድጋፉ ለፖሊሲ እቅድ፣ ቅንጅት እና የኮርፖሬት አገልግሎት አሰጣጥ እና ለፕሮጀክት አስተዳደር እንደሚውል መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
በተጨማሪም ገንዘቡ ለተለያዩ ምክንያቶች ይመደባል ያሉ ሲሆን ፥ የአየር ንብረት ለውጥ፣ የአደጋ ስጋት ቅነሳ ተግባራት እና የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን የሥርዓተ-ፆታ እና የወጣቶች ማጠቃለያ መመሪያዎች እና የውጤት ካርዶች እና ተያያዥ ተግባራት ይውላል ብለዋል፡፡
የአፍሪካ ልማት ፈንድ ለአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሲደግፍ ይህ የመጀመሪያው አለመሆኑ የተነሳ ሲሆን ፥ ከዚህ ባለፈም በርካታ ፕሮጀክቶቹን እንደ የልማት ኤጀንሲ -ኔፓድ፣ በአፍሪካ የመሠረተ ልማት ዝርጋታ መርሃ ግብር፣ የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጠና ሴክሬታሪያት፣ የአፍሪካ የበሽታ መቆጣጠሪያና መከላከያ ማእከል እና የአየር ንብረት ልማት በአፍሪካ ፕሮግራም ማድረጉ ተጠቅሷል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!