አዲስ አበባ፣ የካቲት 9፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) 6ኛው የአፍሪካና የአውሮፓ ሕብረት ጉባኤ “በአፍሪካ-አውሮፓ ኢንቨስትመንት ማዕቀፍ” እንዲሁም በአፍሪካ እና በሌሎች ዓለም አቀፍ አጀንዳዎች ላይ እንደሚመክር ተገለጸ።
የአውሮፓ ኅብረት ጉባኤውን በተመለከተ ባወጣው መግለጫ፥ በጉባኤው አውሮፓ ኅብረትና የአፍሪካ ኅብረት በፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ ስለሚኖራቸው የጋራ ጥቅምን ያስጠበቀ ትስስር በተለይም ሁለቱ አህጉራት የጋራ ብልጽግናን መገንባት በሚችሉባቸው ጉዳዮች ላይ መሪዎቹ ይመክራሉ ተብሎ ይጠበቃል።
የአህጉራቱ መሪዎች “በአፍሪካ-አውሮፓ ኢንቨስትመንት ማዕቀፍ” እና አሳሳቢ በሆኑት የአየር ሁኔታ ለውጥ፥ የሰላምና ደህንነት ጉዳዮችም ላይ እንደሚመክሩ ነው የተገለጸው።
በተጨማሪም ስለ ግብርና ምርትና ምርታማነት፣ አለም አቀፍ ቀውስ እያስከተሉ ስለሚገኙ የጤና ችግሮች ጉባኤው እንደሚመክር መገለጹን የኢዜአ ዘገባ ያመላክታል።
ስድስተኛው የአፍሪካ ኅብረትና አውሮፓ ኅብረት የጋራ ጉባኤ ከነገ ጀምሮ ለሁለት ቀናት በቤልጂየም ዋና ከተማ ብራሰልስ ይካሄዳል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!