አዲስ አበባ፣ የካቲት 12፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ)በቤልጄም ብራሰልስ ሲካሄድ የቆየው 6ኛው የአፍሪካና የአውሮፓ ህብረቶች የመሪዎች የጋራ ጉባኤ መጠናቀቁን ተከትሎ ስምምነት በደረሱባቸው ጉዳዮች ላይ የጉባኤውን የጋራ መግለጫ አውጥተዋል።
ስምንት ነጥቦችን ባካተተው የጥምር ጉባኤው መግለጫ የአፍሪካና የአውሮፓ ህብረቶች አጋርነታቸውን ለማደስና በጋራ ጉዳዮች ላይ ጠንካራ ትብብር ለማድረግ ቁርጠኛ መሆናቸውን ጠቅሰዋል።