የሀገር ውስጥ ዜና

የህዳሴ ግድቡ ኃይል ማመንጨት መጀመር ከፍተኛ ስትራቴጂያዊ ፋይዳ አለው- አምባሳደር መለስ ዓለም

By Feven Bishaw

February 21, 2022

አዲስ አበባ፣ የካቲት 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ኃይል ማመንጨት መጀመሩ ከፍተኛ ስትራቴጂያዊ ፋይዳ እንዳለው እና የኢትዮጵያንና የኬንያን ኤሌክትሪክ ኃይል ትስስር እንደሚያጠናክር በኬንያ የኢትዮጵያ አምባሳደር መለስ ዓለም ተናገሩ።

በኢትዮጵያና በኬንያ መካከል የኃይል ግዢ ስምምነትን የሚከታተል የቴክኒክ ኮሚቴ ስብሰባ በናይሮቢ ከተማ የተካሄደ ሲሆን÷ ታላቁ የህዳሴ ግድብ ኃይል ማመንጨት መጀመሩ ለአካባቢው ሀገራትና ለተቀረው ዓለም ስትራቴጂያዊ ፋይዳ እንዳለው አምባሳደር መለስ አስረድተዋል፡፡