አዲስ አበባ፣ የካቲት 16፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ለአራት ሬዲዮ ብሮድካስት ባለፈቃዶች የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ሰጠ፡፡
ማስጠንቀቂያ የሰጣቸው ሬዲዮ ብሮድካስት ባለፈቃዶችም ፣ ሟርሴ መልቲሚዲያ ኃ.የተ.የግ.ማ.(ጄ ሬዲዮ ጣቢያ 106.7 ) ፣ አዲስ ኦንላይን የግንኙነትና የግብይት ሥራ ኃ.የተ.የግ.ማ.(ሀበሻ ኤፍ.ኤም. ሬዲዮ 98.7) ፣ትርታ ትሬዲንግ ኃ.የተ.የግ.ማ. (ትርታ ሬዲዮ 97.6) እና ኢትዮ ዋርካ መልቲ ሚዲያና ኮሙኒኬሽን አ.ማ (ዋርካ ሬዲዮ 104.1) መሆናቸው ተገልጿል፡፡