የሀገር ውስጥ ዜና

የብልጽግና ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ሲያካሂድ የነበረውን ስብሰባ ዛሬ አጠናቀቀ

By ዮሐንስ ደርበው

February 24, 2022

 

አዲስ አበባ፣ የካቲት 17፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የብልጽግና ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ላለፉት ሁለት ቀናት ሲያካሂድ የነበረውን ስብሰባ ዛሬ አጠናቀቀ።

ኮሚቴው በወሳኝ አገራዊና የፓርቲ ሥራዎች ላይ ተወያይቶ በቀጣይ ስለሚከናወኑ ተግባራት አቅጣጫ ማስቀመጡን የብልጽግና ፓርቲ ዋና ጽ/ቤት ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በላከው መግለጫ ጠቁሟል።