የሀገር ውስጥ ዜና

አምባሳደሮች የተሰጣቸውን ተልዕኮ የሚመጥን ስራ አሟልተው መስራት አለባቸው – አቶ ደመቀ መኮንን

By ዮሐንስ ደርበው

February 24, 2022

አዲስ አበባ፣ የካቲት 17፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አምባሳደሮች የተሰጣቸውን ብሄራዊ ተልዕኮ የሚመጥን ስራ አሟልተው መስራት እንዳለባቸው ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን አሳሰቡ።

አቶ ደመቀ ይህን ያሉት በቅርብ ለተሾሙ አምባሳደሮች እየተሰጣቸው ባለው ስልጠና ላይ ነው።

ኢትዮጵያን ወክለው በተለያዩ ሀገራት የሚሰማሩ አምባሳደሮች ተለዋዋጭ የሆነውን የአለምን ፍላጎት ከግምት ባስገባ መልኩ በቂ ዝግጅት አድርገው ተልዕኳቸውን በአግባቡ መወጣት እንዳለባቸው ተናግረዋል።

የሚሄዱበትን አካባቢም በደንብ በማወቅና በመቃኘት ለሀገሪቱ ብሄራዊ ጥቅም መከበር በተለየ ትኩረት መስራት እንዳለባቸው ነው ያሳሰቡት፡፡

ባለፈው አንድ ዓመት የኢትዮጵያን ሉዓላዊ ክብር የተዳፈሩ የዲፕሎማሲ ጫናዎች እንደነበሩ ጠቁመው÷ ያልተገቡ ጫናዎችን ሁሉ በህዝብና ዳያስፖራው ጠንካራ ድጋፍ በፀጥታ ኃይሎች ተጋድሎና በመንግስት ጠንካራ አቋም ተሻግረናቸዋል ብለዋል።

በቀጣይም የሚገጥሙንን ፈተናዎች የሀገራትን ተለዋዋጭ ፍላጎት እያስተዋልን ጠንካራ ስራ መስራት ይገባናል ነው ያሉት፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!