የሀገር ውስጥ ዜና

የምስራቅ ዕዝ የሜዳሊያ ሽልማትና የማዕረግ ማልበስ ሥነሥርዓት አካሄደ

By Mekoya Hailemariam

February 26, 2022

አዲስ አበባ፣ የካቲት 19፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት የምስራቅ ዕዝ የሜዳሊያ ሽልማትና የማዕረግ ማልበስ ሥነሥርዓት አካሄደ።

በሰመራ ከተማ እየተካሄደ ባለው ስነ ስርዓት ላይም የጦር ሃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላን ጨምሮ የጦሩ ከፍተኛ አመራሮች መገኘታቸውን ከመከላከያ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

በመርሃ ግብሩ ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ÷ “ታሪካዊ ጠላቶቻችን ከውስጥ ባንዳዎች ጋር ተባብረው ሀገራችንን ለማፍረስና ህዝባችንን ለመበታተን የደቀኑብንን አደጋ በመቀልበሱ ሂደት የምስራቅ ዕዝ አኩሪ የጀግንነት ታሪክ ፈፅሟል” ብለዋል።

ግዳጃችን አላለቀም ያሉት ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ፥ ለቀጣይ ተልዕኮ ከዕለቱ ተሻላሚዎችም ሆነ እነሱን ካፈራው ምስራቅ ዕዝ የበለጠ ሐይል ማደራጀት ፣ መሠልጠን ፣ መዘጋጀት እንደሚጠበቅ ጠቁመዋል።

ኢታማዦር ሹሙ ለሀገር ባለው ፍቅሩ የሚታወቀው እና ኢትዮጵያን በመጠበቅ አኩሪ ታሪክ ላለው የአፋር ህዝብና ከአብራኩ ለወጡ ልዩ ሐይሎችና ሚሊሻ አባላት ከምስራቅ ዕዝ ጋር በአጋርነት ለፈፀሙት ጀግንነት እና ለነበራቸው ፅናት ምስጋና አቅርበዋል።

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!