የሀገር ውስጥ ዜና

አሸባሪው ሸኔ በሚንቀሳቀስባቸው አካባቢዎች የተቀናጀ እርምጃ እየተወሰደበት መሆኑ ተገለጸ

By Feven Bishaw

February 28, 2022

አዲስ አበባ፣ የካቲት 21፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በቄለምና ምዕራብ ወለጋ እንዲሁም አሸባሪው ሸኔ በሚንቀሳቀስባቸው ሌሎች አካባቢዎች የተቀናጀ እርምጃ እየተወሰደ መሆኑን የኦሮሚያ ክልል ፀጥታና አስተዳደር ቢሮ ገለጸ።

በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ ዞኖች አርሶ አደሮችንና ሌሎች ሰላማዊ ወገኖችን ጭምር በመግደል፣በመዝረፍና በማገት አሸባሪው ሸኔ በህዝብ ላይ የከፋ ችግር እያደረሰ ይገኛል።